top of page
Support Group

GRENFELL DEDICATED SERVICE

If you or a bereaved family member or survivor and would like to access further information

about your service, please click below to login

የአገልግሎት ንድፍ

ዴዲኬትድ ሰርቪስ (Dedicated Service) ከግሬንፌል (Grenfell)  ህንጻ አሳዛኝ አደጋ ለተረፉ እና ቤተሰቦቻቸውን ላጡ በነፍስ ወከፍ ሁሉን ያማከለ አገልግሎት ያቀርባል። በNHS እና በአካባቢው ምክር ቤት ጥምረት የሚሰጠው ይህ አገልግሎት የሰዎችን የግል ፍላጎት ለማሟላት የተመቻቸ እና ሰዎቹ ለማገገም በሚያደርጉት ጉዞ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነው።  

 

ቤተሰቦቻቸውን ካጡና ከአደጋው ከተረፉት ሰዎች ጋር በቅርብ ጥምረት የታቀደው ዴዲኬትድ ሰርቪስ በጁላይ 2019 ለግሬን ፌል የማገገሚያ ስልት ማዕከላዊ ክፍል በመሆን ተጀምሯል። ቤተሰቦቻቸውን ካጡና ከአደጋው ከተረፉት ሰዎች ተወካዮች የተወጣጣ የመሪዎች ቡድን አገልግሎቱን እየቀረጸ ይገኛል። 

 

ስለ አገልግሎቱና ሰፋ ስላሉ የማገገሚያ ጥረቶች ተጨማሪ መረጃ በ( RBKC ድህረጽ) እና በ(NHS ድህረገጽ) ላይ ይገኛል።

Hands Up

ምን እንጠብቅ

ቤተሰቦቻቸውን ያጡና ከአደጋው የተረፉት ሰዎች ቁልፍ የሆኑ ጥያቄዎቻቸውና ሃሳቦቻቸውን ለመመለስ ተጠሪ ከሚሆናቸው ስመ ጥር ዴዲኬትድ ሰራተኛ ድጋፍ አላቸው። በግል ከሚደረገው አቅርቦት በተጨማሪ ከባለሙያዎች የተወጣጣ ቡድን አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነትን፣ መልሶ መቋቋምንና ትምህርትን የሚሸፍን ድጋፍ ያቀርባል። ቤተሰቦቻቸውን ያጡና ከአደጋው የተረፉት ሰዎች የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟሉ መጠነ ሰፊ የሆኑ አገልግሎቶችን እንደሚያገኙ ለማረጋገጥ ማዕከላዊ እውቅና ያላቸውና ብቁ የሆኑ አገልግሎት መረቦች በዚህ ዙሪያ ሽፋን ይሰጣሉ።  

 

ሰዎች በሚቀበሉት ድጋፍ ዙሪያ የተቻለውን ያህል ምርጫ እና ቁጥጥር እንዲኖራቸው ማድረግ እንዲሁም ባህላዊ ተገቢነት ያላቸውን አገልግሎቶች ማቅረብ የሁል ጊዜ ዓላማችን ነው።  

Working Together

ቡድኑ

 ዴዲኬትድ ሰርቪስ በNHS እና በአካባቢው ምክር ቤት ጥምረት ይሰጣል። አጋርነትን በተመለከተ በሀይለኛ ድንጋጤ እና በቤተሰብ እጦት ጉዳት ዙሪያ የሰለጠነ እንዲሁም በኩባንያዎች ብዝሃነት እና ምርጥ ልምምድ ላይ ለመገንባት ያለመ ቅይጥ ቡድን አለን። ይህም የአካላዊ ጤና ተባባሪ ባለሙያዎችን፣ ቅድመ እንክብካቤ ባለሙያዎችን፣ የአእምሮ ጤና ልምድ ባለሙያዎችን፣ ብቁነት ያላቸውን ማህበራዊ ሰራተኞችን፣ ልምድ ያላቸውን የመልሶ ማቋቋም መኮንኖችን፣ የምክር ባለሙያዎችን፣ ወጣት ሰራተኞችን፣ ብቃት ያላቸውን አስተማሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ባለስልጣኖች ያካትታል። ከዚህ በተጨማሪ ከተለያዩ የማህበረሰብ አጋር ከሆኑ ባለሙያዎች ጋር እንሰራለን። 

Holding Hands

CONTACT US

Thanks for submitting!

bottom of page